Saturday, January 28, 2023

አደባባይ እየውጣ ያለው የብልጽግና ስውር እጅ በቡኖ በደሌ

የቡኖ በደሌ ዞን አስተዳደር አቶ አማን ደኑ እና የዞኑ ድርጅት ቢሮ ኃላፊ አቶ አረጋ ሽጉጤ የበደሌ ወረዳ ሊቃነ ካህናት መላከ ብርሃንን፣ ቀሲስ አያሌው ነጋን እና ቀሲስ እንዳለው ከበደን ቢሮ ጠርተው ለቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተመደቡትን ሰው (በሕገ ወጥ የተሾሙትንና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ግለሰብ) መቀበል እንዳለባቸው ለዚህም የፕሮቴስታንት እና ሙስሊም ወጣቶችን አደራጅተናል፤ እስከ ጅማ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲመቻች አድርገናል በማለት በግድ እንዲቀበሉ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛል።



አቶ አማን ደኑ
አቶ አረጋ ሽጉጤ




የምእራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት በሕገ ወጥ የተሾሙትንና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ግለሰብ ለመቀበል በሚል ለብልጽግና ባለስልጣናት ጥሪ ማስተላለፍ ጀምረዋል።

የምእራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት ግምቢ ከተማ መንበረ ጵጵስና ቤተ ክህነት ሃላፊ የሆኑት ሀብታሙ በንቲ በሕገ ወጥ የተሾሙትንና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ግለሰብ ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነና በአቃባበሉ ላይ ለብልጽግና ባለስልጣናት የጥሪ ደብዳቤ መላክ ጀመረዋል። ይህ ሃገረ ስብከት በብጹእ አቡነ ሩፋኤል የሚመራ ሲሆን በቃል የተናገሩትን በተግባር እርምጃ በመውሰድ የሚያሳዩበት ትልቅ ስራ ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።




Friday, January 27, 2023

አደባባይ እየውጣ ያለው የብልጽግና ስውር እጅ

  •  በቅዱስ ሲኖዶስ ተውግዞ የተለየው ቡድን ዛሬ ከኦሮሚያ ክልል ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ጋር በዝግ ውይይት እያደረጉ ይገኛል። የውይይቱን ይዘት እንደደረሰን ይዘን እንመጣለን።
  •  “መቀመጫችሁን አዲስ አበባ ማድረግ አለባችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን።” ሺመልስ አብዲሳ
  •  አዲስ አበባና በአዲስ አበባ ያሉ አድባራትና ገዳማትን በቀጣይ የግጭት ቀጠና ለማደርግ እየተሰራ ይገኛል።

 በቅዱስ ሲኖዶስ ተውግዞ የተለየው ቡድን መቀመጫ መንበራቸውን በወለጋ ለማድረግ አስቀድመው ባቀዱት መሰረት እየተንቀሳቀሱ የነበረ ቢሆንም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ በኦሮሚያው ፕሬዝዳንት በተሰጠ መመሪያ በአዲስ አበባ እንዲያደርጉ ታዘዋል። ይህም በቀጣይ የቤተ ክርስቲያንን ሃብት መካፈል አለብን በሚል ሰበብ አዲስ አበባንና በአዲስ አበባ ያሉ አድባራትና ገዳማትን የግጭት ቀጠና ለማድረግ እየሰሩ ይገኛል።

ዘግይቶ በደረሰን መረጃ ሕገወጥ ሿሚዎቹና ተሿሚዎቹ ከሹመቱ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደደረሱ ለደህንነታቸው አመች ነው በማለት ከኋላ ሁኖ በሚዘውራቸው የብልጽግና መንግስት በተዘጋጀላቸው በኦሮሚያ ጠቅላይ ፖሊስ መምሪያ በሚገኝ ማረፊያ አስቀምጧቸው እንደነበር ታውቋል። በኋላ ላይ ለምን ወደ ሆቴል እንዲዛወሩ እንደተደረገ የታወቀ ነገር የለም።




በኢትዮጵያ/ኦ/ቤ/ክ በምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ቄስ ለታ ደገፌ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ሕገ ወጥ አካላትን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ ነው።

በኢትዮጵያ/ኦ/ቤ/ክ በምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ቄስ ለታ ደገፌ ጥር 20 ቀን ሕገ ወጡን ቡድን ለመቀበል  በጊምቢ ከተማ በመዘዋወር በሞንታርቦ ታግዘው ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። የድምጽ ቅጁም ትርጉም እንደሚከተለው ነው።

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።”  ገላትያ 5፥1

የኦሮሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ! እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ማለትን እንፈልጋለን። የምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት ፣ ጊምቢ ከተማ ፣ በጊምቢ ከተማ ለሚትኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይዎች እና ለሌሎችም ለሁሉም ፤ ብፁዓን አባቶቻችን በጥር 14 ቀን ከኦሮሚያ ይነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች በሙሉ መልስ የተሰጠበት ከ20 የሚበልጡ ጳጳሳትን የሾምን ፣ ኦሮሚያ ውስጥ ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት መልስ የሰጡበት ያችን የተከበረች የተባረከች ቀን። ታዲያ ከእነዚህ ብፁዓን አባቶች ውስጥ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ለምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የተሾሙት በጥር 20 በዕለተ ቅዳሜ ከብፁዓን አባቶች ጋር ብዙ ሆነው ወደ ጊምቢ ከተማ ይመጣሉ። ሁላችሁም ወጥታችሁ እንዲትቀበሏቸው በዚህ ደስታችን ላይም እንዲትገኙ በእግዚአብሔር ስም ልናሳስባችሁ እንፈልጋለን። በኦሮሚያ ለሚገኙ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሉ ለብዙ ዘመናት ይጠየቅ ለነበረው ጥያቄ መልስ ተሰጥቶበታል። የኦሮሚያ ቅዱስ ስኖዶስ እነዚህን ጥያቄዎች በመስማት በኦሮሚያ ለሚገኙ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሉ መልስ ለመስጠት ጳጳሳትን እየሾመ ይገኛል። ለኦሮሚያ የተሾሙት ከ20 የሚበልጡ ጳጳሳት በቀን ጥር 20 በዕለተ ቅዳሜ በጊምቢ ከተማ አደራሽ ይገኛሉ። ሌሎች አማኞችም በዚህ ደስታችን ላይ እንዲትገኙ የተደሰትንበትን እንዲትደሰቱልን በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናቀርብላችኋለን። በድጋሚ እንኳን ደስአላችሁ ደስአለን ማለት እንፈልጋለን። የኦሮሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ! የምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት እንኳን ደስአላችሁ ደስአለን።"




Thursday, January 26, 2023

የሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስና መሐንዲሶች

የዘር ፖለቲካ በሀገራችን ማቀንቀን ከጀመረ ሦስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ረጅም ጊዜ ውስጥ ጽንፈኛ ኃይሎች የመጀመርያ ኢላማቸው ካደረጓቸው ተቋማት ውስጥ አንደኛዋና ዋነኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ በግልጽ የሚታይ ሀቅ ነው።

እንደማሳያ ጥምጣማቸውን ጠምጥመው ለአገልግሎት የሚንቀሳቀሱ ካህናት አባቶችን እንደ ሃይማኖት አባት ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ካድሬ እንዲቆጠሩ ለማድረግ እንዲህ እያሉ የማጠልሸት ሥራ ሲሰሩ ቆይተዋል።  "dabbale mata addii biyya keenyarra badii." ትርጉሙ "ነጭ ራስ ካድሬ ከሀገራችን ጥፋ።" እና ወዘተ በማለት የዋኹን ምዕመን ከእምነቱ ለማስኮብለል ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።

በተለይ የፖለቲካ ርዕዮታቸውን ለማራመድ የተመቻቸው እና የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክታቸውን የተቀበላቸውን የምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና በአሁኑ አከላለል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ምዕመናን ተጠቃሽ ናቸው። ሆኖም ግን ባሰቡት ልክ በፖለቲካቸው ተጠልፈው እምነታቸውን ለቀው መናፍቅ ወይ ሙስሊም አልሆኑም። በዚህ የተበሳጩት ፖለቲከኞች ተልእኳቸውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሰርጎ ገቦችን በመመልመል  በፖለቲካቸው አጠመቋቸው።

ማመናቸውን ካረጋገጡ በኋላ እንዲታመኑ ግዳጅ ሰጧቸው። ከእነዚህ ምልምሎች አንዱ የሆነው ዋሲሁን አመኙ ሲሆን ይህ ግለሰብ ከሃይማኖቱ ይልቅ ለዘሩ የሚንጨረጨር፣ ናርሲሲት፣ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ አሁን ቤተክርስቲያንን ለመክፈል ህገ ወጥ ጳጳሳት እንዲሾሙ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ሲታገል የኖረው ምንም እውቀት ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ ጵጵስና እንዲሾሙ በተለይ ሁለት መነኮሳትን የመለመለ ፀረ ኦርቶዶክስና ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ግለሰብ ነው።

ፖለቲከኞቹ የሚሹትን ከሀገር የመከፈል ፍላጎት በቤተክርስቲያን በኩል ማሳካት ይቻላል ብሎ የሚያምው ዋሲሁን አመኙ፣ ለዚህ ዓላማው መሳካት ከዕውቀት ነፃ የሆኑ፣ የኢኮኖሚ እና የስነምግባር ችግር ያለባቸውን በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ያሉትን ካህናትና ዲያቆናትን በመመልመል በደካማ ጎናቸው እየገባ ለሰይጣናዊ ተግባሩ የሚጠቀም ግለሰብ ነው። መንግስት የሃገሪቱ ሕዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ፖሊሲ በማውጣቱ ምክንያት በምእራብ ወለጋ ያሉ ምእመናን ቅዳሴውን ሰምተው አሜን ማለት አለመቻላቸውን ያስተዋለው ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በእራሳቸው ተነሳስተው ከሚቀድሱ ብሎ በቅንነት በማሰብ ቅዳሴውን ተርጉሞ ሲሰጣቸው የሰው ሀሳብ በመስረቅ እና በፖለቲካ አክራሪነታቸው የሚታወቀው ምትኩ ተኮላ የሚባል ሰው (በነገራችን ላይ ይህ ግለሰብ "ኦሮሞና ኦርቶዶክስ" የሚል መጽሐፍ ጽፎ የኦርቶዶክስ ተወሕዶ ሃይማኖትን ከባህላዊው ዋቄፈና እምነት ጋር አቻ ለማድረግ የጣረ ለስሙ ቄስ ነኝ የሚል ዘረኛ ነው) ጋር በመሆን ዲ/ን ዳንኤል የተረጎመውን የኦሮምኛ ቅዳሴ ከኤች አይ ቪ መከላከያና መቆጣጠርያ በዘረፈው ገንዘብ አሳትሞ በማሰራጨት የሚታወቅ የአዕምሮ ሀብት ሌባም ነው። ይኼ ሰው ነው እንግዲህ ቤተክርስቲያንን ለሁለት ለመክፈል ሲጥር የቆየውና ጊዜው የኛ ነው በሚል ስሜት እና በማን አለብኝነት ህገ ወጥ ሿሚና ሹመኞች ፊት ፎቶ በመነሳት ፖለቲካዊ የመገንጠል ግቡን አሳክቼያለኹ በሚል አጋንንታዊ መንፈስ የሚጀነነው። ይቆየን እንመለስበታለን



ሰበር ዜና

  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሕገ ወጥ ጵጵስና ሿሚዎችንና ተሿሚዎችን አወገዘ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሳያውቀውና ሳይመክርበት በግል ፍላጎታቸው ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመናል በማለት መግለጫ ያወጡትን ሦስት ሊቃነ ጳጳሳትና ሕገ ወጥ ሹመት የተቀበሉ መነኮሳትን አውግዞ ለይቷል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ያልተወሰነ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን የመክፈል ሴራ የጠነሰሱት ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ልብ ገዝተው በይቅርታ ልብ ወደ ቤተ ክርስቲያን እስከሚመለሱ ድረስ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ተለይተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ያለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ሲመተ ጵጵስናን በጓሮ በር ለማግኘት የቋመጡት ሕገ ወጥ ተሿሚዎችም በውግዘት እንዲለዩ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል።



የጨለማው ቡድን ቀጣይ ዕቅድ

ካፈርሁ አይመልሰኝ በሚል ድርቅና ቅዱስ ሲኖዶስ በድርድር "የሾምናቸውን ኤጲስ ቆጶሳት" ካልተቀበለን የራሳችንን ፓትርያርክ መርጠን ንብረት ወደ መካፈል እንሔዳለን እያለ ያለው የእነ "አባ" ሳዊሮስ ቡድን ሌላ ሕገወጥ ሹመት ሊሰጥ መሆኑ ተሰምቷል።

ለዚህም ዓላማ ከተለያዩ ቦታዎች ሹመት ናፋቂ "መነኮሳትን" ሕገወጥ ቡድኑ ወደሚሰበሰብበት ቦታ እንዲከቱ ጥሪ ተላልፎላቸው በመግባት ላይ ይገኛሉ።


የሌባ በሩ ጓሮ፣ ቀኑ ሌሊት

የብልጽግና መንግሥት ከበር ይልቅ በጓሮ በኩል ለመግባት በስመ ጵጵስና የመጡትን የሹመት ሌቦችን ለማደራደር ሌሊቱን ቀን እያደረገ ቤተ ክህነቱን በምሽት መውረር ተያይዞታል። ትናንት ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽትም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቤት በመግባት የማግባባትና የማስፈራራት ሥራ ሲሠራ አምሽቷል። ሹመኞቹ በጓሮ ለመግባት የሚያደርጉትን የሌብነት ሩጫ ጨለማን ተገን ያደረጉ የመንግሥት ጀሌዎች የማግባቢያ መሰርሰሪያ ይዘው መግቢያ ቀዳዳ ሲፈልጉ በማደር ላይ ናቸው። ማስፈራሪያው በብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት ላይ ብቻ ሳይወሰን አባ ገብረ ሥላሴን (አባ ሕጻን) መረጃ ለምን አወጡ በሚል ከፍተኛ ማዋከብ እያደረሰባቸው ይገኛል።





የሚዲያው አርበኛ

በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ የኦሮሚያ ቤተክህነት መንበረ ጵጵስና ለማድረግ በቅድስተ ቅዱሳን ካቴድራል ሰሪቲ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

በመጪው ቅዳሜ ጀሌዎቻቸውን አቀባበል እንዲያደርጉላቸው በአቡነ ሩፋኤል ትእዛዝ ሰጭነት ጥር 21 ቀን የእመቤታችን በዓለ ንግሥ ላይ ሹመታቸውን ለማወጅ በደብሩ ይገኛሉ፡፡
አስቀድመው ያደራጁትን ወጣቶች መዝሙር እንዲያጠኑ አድርገዋል፡፡ ለዚህም የክልሉ መስተዳደር ጥበቃና ፈቃድ እንደሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቡነ ሩፋኤል በምዕራብ ወለጋ ምዕመናን እና ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሙትን ግፍና ሴራ በዝርዝር እንመለሳለን፡፡



Wednesday, January 25, 2023

የውስጥ አርበኛ ሆነው እየሠሩ ያሉት ቀሲስ በላይ መኮንን ወደ ተለያዩ ሃገረ ስብከቶች ሕገወጡን ቡድን እንዳይቀበሉ ተገልጾ የተጻፈውን ደብዳቤ አልፈርምም አሉ፡፡

ከመጀመሪያው ጀምረው የኦሮሚያ ቤተክህነት ካልተመሠረተ ብለው ሲየደራጁ የነበሩት እና ኋላ ጥያቄያችን መልስ አግኝቷል በማለት የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው እየሠሩ ያሉት ቀሲስ በላይ መኮንን የውስጥ አርበኛ በመሆን ራሱን ላደራጀው አካል ከፍተኛውን ሚና እየተጫወቱ ሲሆን ከጠቅላይ ቤተክህነት ሕገወጡን አካል እንዳይቀበሉ የሚገልጽ ወደየ ሀገረ ስብከቶች እንዲላኩ የተጻፉ ደብዳቤዎችን አልፈርምም በማለት ተቃሞዋቸውን ከወዲሁ ጀምረዋል፡፡ በቤተ ክህነቱ አስተዳደር ጉባኤ እና በሌሎች ብጹአን አበው የሚደረጉ ሕግን የማስከበር ሥራዎችንም ለሕገወጡ ቡድን ከውስጥ የሚያቀብሉት እሳቸው እንደሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡



ሰበር ዜና

በመንግሥት ለሽምግልና በሚል ኮሚቴ አቋቋመ

****************************************************
የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት በሚጥስ መልኩ በሕገወጥ ሲመት ላይ የተሳተፉ ጳጳሳትን አስታርቃለሁ በሚል መንግስት አስቀድሞ ያቀደውን መፈንቅለ ሲኖዶስ ለማስፈጸም ይረዳው ዘንድ ለሽምግልና ኮሚቴ አቋቋመ። የኮሚቴው አባላትም ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣የመከላክያ ሚኒስቴሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ አቡነ ሩፋኤል፤ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ አባ ወልደ ኢየሱስ /አባ ሕፃን/ መሆናቸው ተረጋግጧል።



ሰበር ዜና

መንግስት ብጹዓን አባቶችን ማስፈራራቱን ቀጥሎበታል!!

******************************************************
የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ተመስገን ጥሩነህና የመከላክያ ሚኒስቴሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ የሆኑትን ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለንና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ስራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በማስከተል ወደ ቋሚ ሲኖዶስ መግባታቸውን አረጋግጠናል። መንግስት ለችግሩ ፈጣሪዎች ጥበቃና ከለላ እያደረገ ለቤተ ክርስቲያን ሕግና ስርዓት መከበር የቆሙት አባቶች ላይ ጫና መፍጠሩን ቀጥሎበታል።




ሰበር ዜና - ባቶ ደጋጋ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በታጠቁ ሃይሎች ተቃጠለ

ባቶ ደጋጋ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከአዳማ 26 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከአዋሽ መልካሳ ወደ ሶደሬ ሪዞርት በሚወስደው መንገድ በስተግራ ገባ ብሎ የሚገኝ ሲሆን ትላንት ማታ ቁጥራቸው በርከት ባሎ የታጠቁ አካላት ቤተክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል። እሳቱ አሁንም ድረስ አልጠፋም። ለአንድ ሰዓት የቆየ ተኩስ በመተኮስ የአካባቢው ምዕመናን ወደ ቦታው እንዳይጠጉ ሽብር ሲፈጥሩ ቆይተዋል።



የመስተሳልቃን መንበርና የክፉዎች ምክር

 የመፈንቅለ ሲኖዶሱ መሪ ተዋናዮች ነገ በሚጀምረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ካልተገኘን እና ጉዳዩ በድርድር የማያልቅ የራሳችን ፓትርያርክ እንመርጣለን የሚል የማስፈራሪያ መልእክት በመንግሥታቸው በኩል በመላክ ላይ ናቸው።

መፍቀሬ ሲመት ያናወዛቸው ተጨማሪ ሕገወጦችንም "ለመሾም" በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ይህ ሁሉ ጭንቀት የወለደው ዛቻና ግብታዊነት በራሳቸው ሳይሆን በኅቡዕ ቡድን የሚመሩ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው። ዳሩ ግን ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ እንጂ ሊያሸንፉ አይችሉም። የራስን ድርሻ መወጣት ግን መዘንጋት የለበትም።



Tuesday, January 24, 2023

ሰበር መረጃ


የመፈንቅለ ሲኖዶሱ መሪ መንግሥት ራሱ መሆኑን ገለጠ።

ሦስቱን ሊቃነ ጳጳሳት እጅ አድርጎ ሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስና ያሰጠው እና መፈንቅለ ሲኖዶስ ለማድረግ በመጣር ላይ የሚገኘው የብልጽግና መንግሥት የቤተ ክህነቱን ጥበቃ ፖሊሶች አንሥቷል።
በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ሕገወጥ ሲመተ ጵጵስና ሲሰጡ የነበሩት ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት በነገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ለማስገደድ ደኅንነቶቹን አሠማርቷል። ደኅንነቶቹም ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ መኖሪያ ገብተው ይህን እንዲያደርጉ ትእዛዝ ቢያስተላልፉም ቅዱስ አባታችን በሕይወት እያለሁ ሊፈጸም አይችልም ብለው ቁርጥ አቋማቸውን አሳውቀዋቸዋል።
በዚህ ሰዓት ቤተ ክህነቱ ዙሪያውን በፌደራል ፖሊስ ተወርሯል። ይህም የተውኔቱ ደራሲና ከያኒ ራሱ መንግሥት መሆኑን የሚረጋገጥ ሁነት ነው።



የነ"አባ" ሳዊሮስና ሕገ ወጡ ቡድን ቀጣይ እንቅስቃሴዎች

ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ቅዱስ ሲኖዶስን በመዳፈር  በ14/05/2015 ዓ.ም “ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመናል”  ያለው ቡድን አባላት በዛሬው ዕለት (ጥር 16/05/2015 ዓም) አሸዋ ሜዳ አካባቢ ከተወሰኑ ሰዎች ጋር ተሰብስበው ሲመክር  አርፍዷል። በነገው ዕለትም ይህ ሕገ ወጥ ቡድን በኦሮሚያ ባሕል አዳራሽ እንደሚሰባሰብ የታወቀ ሲሆን የጨረቃ ጳጳሳቱን በመደቡባቸው አህጉረ ስብከቶች ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ የተለያዮ ሹመቶችና ምደባዎችን ለማድረግ ያለመ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል።






እየዳኸ ወርኃ ጥር የደረሰው መፈንቅለ ፓትርያርክ (የቀጠለ)

 ጥር 11 ቀን ታቦተ ሕጉ ከገባ በኋላ በግምት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ገዳሙን ኦነግ ሸኔ በመውረር 4 የአካባቢ ተወላጅ ተማሪዎችን ትተው 11ዱን እና የገዳሙን አበምኔት ይዘው በመሔድ ዝቋላ አካባቢ ሲደርሱ አንተ ነፍጠኛ በገዳሙ ውስጥ በአማርኛ እና በግእዝ እንዲቀደስ የምታደርገው ለምንድን ነው በማለት ካንገላቷቸው በኋላ በአንድ በኩል ከእናታቸው ወገን ኦሮሞ እንዳል ሲያረጋግጡ አንተ የእኛ ወገን ስለሆንክ ከእንግዲህ በኦሮምኛ ብቻ እንዲቀደስ አድርግ በማለት እንደለቀቋቸው ለማወቅ ተችሏል።

ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ባፈነገጠ መንገድ ጵጵስና ለመሾም ቀጠሮ ይዘው የነበረው ጥር 16 ቀን ሲሆን ቍጥሩም ከ40 እስከ 50 የሚደርስ የነበረ ሲሆን ለሲመት የተመረጠውም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ነበር ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይሾማሉ ከተባሉ አባቶች ጥቂት የማይባሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ቦታውም ከደብረ ሊባኖስ ወደ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሶዶ ዳጬ ወረዳ በሚገኘው ቢትወደድ ባሕሩ አብርሃም አሠርተው ኅዳር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከ7 ጳጳሳት ጋር በመረቁት ሐሮ ቅዱስ ባለወልድና ቅዱስ ዑራኤል ገዳም 26 መነኰሳትን “ኤጲስ ቆጶስ” ብለው፣ 10 ካህናትን እና 72 ዲያቆናትን ጨምረው መሾማቸው ታውቋል።

ሲመቱን የፈጸሙት ሦስቱ ጳጳሳት ቢሆኑም ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልም እንደ አባ ገብረ ኢየሱስ ኢፋ ያሉ መነኰሳትን መልምለው በመላክ እና ጉዳዩን በስልክ በመከታተል ያደረጉት ተሳትፎ ከፍተኛ እንደ ነበር የመረጃ ምንጮቻችን ገልጠውልናል። ከዚህ በተጨማሪ አጥቢያ ያላቸው መነኰሳት ለመሾም 500,000,00 (አምስት መቶ ሺህ) ከፍለው የተሾሙ ሲሆን በሠራዊት ታጅበው አዲስ አበባ የገቡ መሆናቸው ታውቋል።   

 



ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሶዶ ዳጬ ወረዳ የሚገኘው ሐሮ ቅዱስ ባለወልድና ቅዱስ ዑራኤል ገዳም


 

እየዳኸ ወርኃ ጥር የደረሰው መፈንቅለ ፓትርያርክ

ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ሲኖዶስ በኋላ ሦስቱ ጳጳሳት፣ በጉዳዩ ላይ እጃቸው ያለበት አንዳንድ የብልጽግና ባለሥልጣናት፣ ከቀሲስ በላይ ጋር የኦሮምያ ቤተ ክህነት አንቀሳቃሽ የነበሩ አንዳንድ አካላት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የአቡነ ኤዎጣቴዎስ መኖሪያ ቤት ውስጥ እየተሰበሰቡ ይመክሩ ነበር። ጉዳዩን በበላይነት ይመራ የነበረው የኦሮምያ ቤተ ክህነት አቀኝቃኝ የነበረውና ከእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ጋር በመሆን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያኔ ተመለስኩ ብሎ የነበረው ዋሲሁን አመኑ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን ገልጠውልናል።

መፈንቅለ ፓትርያርክ አድራጊዎቹ በተለይ ከኅዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ቀኑን ሙሉ ተሰብስበው ይውሉ የነበረ ሲሆን ኅዳር 21 ቀን 11፡00 ሰዓት አካባቢ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ወጥተው አንድ አሳቻ ቦታ የኦነግ መስራች፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀኝ እጅ ከሆነው፣ በግል ተወዳድሮ የሕዝብ እንደራሴዎች አባል ከሆነው ከዲማ ነገዎ ጋር ተገናኝተው በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ ባይታወቅም መወያየታቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልጠውልናል።

 



ዶ/ር ዲማ ነገዎ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለሕክምና ከአገር ሲወጡ በተቀነባበረ መንገድ ጽላት ሰርቀው ለመውጣት ሙከራ እንዳደረጉ እና ይህ ድርጊት ሲከሽፍ አቡነ ሳዊሮስ አብረዋቸው እንዲሄዱ የተደረገውም በዓላማ አንድም በየጊዜው የሚያደርጉትንና ከእነማን ጋር እንደሚገናኙ፣ ምን እንደሚሠሩ ለመከታተል እና ምክንያት ፈጥሮ ከአገር እንደወጡ እንዲቀሩ ለማድረግ ቢሆንም ፓትርያርክ ማሳደዱ ስላልተሳካ ጥር 14 የተፈጸመውን ድሪጊት ወደ ማስፈጸሙ እንደተሸጋገሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኦሮሞ ብልጽግና፣ የኦነግ፣ የኦፌኮ አባላት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ባሉበት በተደጋጋሚ በስውር እየተሰበሰቡ ይመክሩ የነበረውም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ፓትርያርክ ለማድረግ ሳይሆን ለዓላማችሁ ደጋፊ አልሆንም በማለታቸው እስከ ግድያ እየዛቱባቸው የሚገኙትን ሊቀ ጳጳስ ፕትርክና ለማሾም ብቻ ሳይሆን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አሻሽለው ለእነርሱ በሚመች ማንም ሰው ጳጳሳትን የሚሾምበትን ሕግ ለማስቀመጥ ቢሆንም ሁሉም ተሰብሳቢ ሲስማማ የሰላም ምኒስቴር ዴኤታ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ ብቻ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምን አደረገችን? ተው ይህ ነገር አያዋጣም” በማለት እንደተናገሩም ለማወቅ ተችሏል።

በተደጋጋሚ ይወያይ የነበረው ስውር ቡድን ኅዳር 21 ቀን እንደሁል ጊዜው ዶ/ር አቡን ኤዎስጣቴዎስ መሪነት ወደ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ከመሄዳቸው በፊት ስለአቡነ አብርሃም ይችን ጎጃሜ ወደደችም ጠላችም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ነቅለን እንጥላታለን እኔ ዶክትሬቴን ተምሬ እንግሊዝኛ መናገር የማትችል ጳጳስ እይመራችን፣ አቡነ እስጢፋኖስን አቋም የላትም አስፈራርተን የዓላማችን ተባባሪ እናደርጋለን፣ ይችን ዘፋኝ አዝማሪ ናትናኤልን ዓላማችንን የማትቀበል ከሆነ እናስወግዳታለን፣ ሩፋኤል እሷ ከእኛ ጋር ነች በማለት ሲዝቱ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።  

 



ሽመልስ አብዲሳ

ኅዳር 21 ቀን ከዲማ ነገዎ ጋር የተወያየው አካል በሦስተኛ ቀኑ ኅዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ባለድርሻ የሚሏቸው የኦሮሞ የብልጽግና ባለሥልጣናት፣ ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች፣ የኦነግና የኦፌኮ አመራሮች በአቡነ ሳዊሮስ ሰብሳቢነት በእስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ማድረጋቸውንም ምንጮቻችን ገልጠውልናል። በሦስቱ ጳጳሳት የተደረገው ሲመት የመንግሥት ድጋፍ ያለው ለመሆኑ ሌላው ማሳያ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ሲመቱን ሊቃን ጳጳሳት እንዲያሳምን ከማድረግ በተጨማሪ እኔም ኦርቶዶክስ ነበርኩ አንዳንድ ነገሮች አልመቸኝ በማለታቸው ወጥቼ እንጂ በማለት የማገባባት ስራ እንዲስራ ሀላፊነት የወሰደ እና የኦሮምያ ቤተ ክህነትንም በገንዘብ ይደግፍ እንደነበር ይታወቃል። ሽመልስ አብዲሳ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ የመንግሥት ጋር የተጣላ መስሎ ከአገር የወጣው ድንቁ ደያስ አንድ ሙሉ ሕንፃ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።

አቶ ሌንጮ እና አቶ ገላሳ በሰጡት አንድ ሥልጠና ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአዳማ አዩ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተይዞላቸው ለሦስት ቀን ሲዶለቱ መሰንበታቸው ለማወቅ ተችሏል።

 

 

በሲሞን መንገድ ላይ ተገኙት “አባ” ወ/ኢየሱስ ኢፋ (ፍቅሩ ኢፋ) - ክፍል ሁለት

  እኚህ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን መጀመራቸው አያጠራጥርም። በዚህም የሕይወት ምርጫቸውንም ቅዱስ ጳውሎስ “እንደኔ ብትሆኑ እወዳለኹ” ያለውን ተከትለው በሙሉ ጊዜያቸው እግዚአብሔርን እያመሠ...