የዘር ፖለቲካ በሀገራችን ማቀንቀን ከጀመረ ሦስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ረጅም ጊዜ ውስጥ ጽንፈኛ ኃይሎች የመጀመርያ ኢላማቸው ካደረጓቸው ተቋማት ውስጥ አንደኛዋና ዋነኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ በግልጽ የሚታይ ሀቅ ነው።
እንደማሳያ ጥምጣማቸውን ጠምጥመው ለአገልግሎት
የሚንቀሳቀሱ ካህናት አባቶችን እንደ ሃይማኖት አባት ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ካድሬ እንዲቆጠሩ ለማድረግ እንዲህ እያሉ የማጠልሸት
ሥራ ሲሰሩ ቆይተዋል። "dabbale mata addii biyya keenyarra badii." ትርጉሙ
"ነጭ ራስ ካድሬ ከሀገራችን ጥፋ።" እና ወዘተ በማለት የዋኹን ምዕመን ከእምነቱ ለማስኮብለል ያልፈነቀሉት ድንጋይ
የለም።
በተለይ የፖለቲካ ርዕዮታቸውን ለማራመድ
የተመቻቸው እና የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክታቸውን የተቀበላቸውን የምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና በአሁኑ አከላለል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ
ምዕመናን ተጠቃሽ ናቸው። ሆኖም ግን ባሰቡት ልክ በፖለቲካቸው ተጠልፈው እምነታቸውን ለቀው መናፍቅ ወይ ሙስሊም አልሆኑም። በዚህ
የተበሳጩት ፖለቲከኞች ተልእኳቸውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሰርጎ ገቦችን በመመልመል በፖለቲካቸው አጠመቋቸው።
ማመናቸውን ካረጋገጡ በኋላ እንዲታመኑ
ግዳጅ ሰጧቸው። ከእነዚህ ምልምሎች አንዱ የሆነው ዋሲሁን አመኙ ሲሆን ይህ ግለሰብ ከሃይማኖቱ ይልቅ ለዘሩ የሚንጨረጨር፣ ናርሲሲት፣
የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ አሁን ቤተክርስቲያንን ለመክፈል ህገ ወጥ ጳጳሳት እንዲሾሙ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ሲታገል የኖረው ምንም
እውቀት ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ ጵጵስና እንዲሾሙ በተለይ ሁለት መነኮሳትን የመለመለ ፀረ ኦርቶዶክስና ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ
ግለሰብ ነው።
ፖለቲከኞቹ የሚሹትን ከሀገር የመከፈል
ፍላጎት በቤተክርስቲያን በኩል ማሳካት ይቻላል ብሎ የሚያምው ዋሲሁን አመኙ፣ ለዚህ ዓላማው መሳካት ከዕውቀት ነፃ የሆኑ፣ የኢኮኖሚ
እና የስነምግባር ችግር ያለባቸውን በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ያሉትን ካህናትና ዲያቆናትን በመመልመል በደካማ ጎናቸው እየገባ
ለሰይጣናዊ ተግባሩ የሚጠቀም ግለሰብ ነው። መንግስት የሃገሪቱ ሕዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ፖሊሲ በማውጣቱ ምክንያት በምእራብ
ወለጋ ያሉ ምእመናን ቅዳሴውን ሰምተው አሜን ማለት አለመቻላቸውን ያስተዋለው ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በእራሳቸው ተነሳስተው ከሚቀድሱ
ብሎ በቅንነት በማሰብ ቅዳሴውን ተርጉሞ ሲሰጣቸው የሰው ሀሳብ በመስረቅ እና በፖለቲካ አክራሪነታቸው የሚታወቀው ምትኩ ተኮላ የሚባል
ሰው (በነገራችን ላይ ይህ ግለሰብ "ኦሮሞና ኦርቶዶክስ" የሚል መጽሐፍ ጽፎ የኦርቶዶክስ ተወሕዶ ሃይማኖትን ከባህላዊው
ዋቄፈና እምነት ጋር አቻ ለማድረግ የጣረ ለስሙ ቄስ ነኝ የሚል ዘረኛ ነው) ጋር በመሆን ዲ/ን ዳንኤል የተረጎመውን የኦሮምኛ ቅዳሴ
ከኤች አይ ቪ መከላከያና መቆጣጠርያ በዘረፈው ገንዘብ አሳትሞ በማሰራጨት የሚታወቅ የአዕምሮ ሀብት ሌባም ነው። ይኼ ሰው ነው እንግዲህ
ቤተክርስቲያንን ለሁለት ለመክፈል ሲጥር የቆየውና ጊዜው የኛ ነው በሚል ስሜት እና በማን አለብኝነት ህገ ወጥ ሿሚና ሹመኞች ፊት
ፎቶ በመነሳት ፖለቲካዊ የመገንጠል ግቡን አሳክቼያለኹ በሚል አጋንንታዊ መንፈስ የሚጀነነው። ይቆየን እንመለስበታለን
No comments:
Post a Comment