Tuesday, January 24, 2023

እየዳኸ ወርኃ ጥር የደረሰው መፈንቅለ ፓትርያርክ (የቀጠለ)

 ጥር 11 ቀን ታቦተ ሕጉ ከገባ በኋላ በግምት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ገዳሙን ኦነግ ሸኔ በመውረር 4 የአካባቢ ተወላጅ ተማሪዎችን ትተው 11ዱን እና የገዳሙን አበምኔት ይዘው በመሔድ ዝቋላ አካባቢ ሲደርሱ አንተ ነፍጠኛ በገዳሙ ውስጥ በአማርኛ እና በግእዝ እንዲቀደስ የምታደርገው ለምንድን ነው በማለት ካንገላቷቸው በኋላ በአንድ በኩል ከእናታቸው ወገን ኦሮሞ እንዳል ሲያረጋግጡ አንተ የእኛ ወገን ስለሆንክ ከእንግዲህ በኦሮምኛ ብቻ እንዲቀደስ አድርግ በማለት እንደለቀቋቸው ለማወቅ ተችሏል።

ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ባፈነገጠ መንገድ ጵጵስና ለመሾም ቀጠሮ ይዘው የነበረው ጥር 16 ቀን ሲሆን ቍጥሩም ከ40 እስከ 50 የሚደርስ የነበረ ሲሆን ለሲመት የተመረጠውም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ነበር ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይሾማሉ ከተባሉ አባቶች ጥቂት የማይባሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ቦታውም ከደብረ ሊባኖስ ወደ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሶዶ ዳጬ ወረዳ በሚገኘው ቢትወደድ ባሕሩ አብርሃም አሠርተው ኅዳር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከ7 ጳጳሳት ጋር በመረቁት ሐሮ ቅዱስ ባለወልድና ቅዱስ ዑራኤል ገዳም 26 መነኰሳትን “ኤጲስ ቆጶስ” ብለው፣ 10 ካህናትን እና 72 ዲያቆናትን ጨምረው መሾማቸው ታውቋል።

ሲመቱን የፈጸሙት ሦስቱ ጳጳሳት ቢሆኑም ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልም እንደ አባ ገብረ ኢየሱስ ኢፋ ያሉ መነኰሳትን መልምለው በመላክ እና ጉዳዩን በስልክ በመከታተል ያደረጉት ተሳትፎ ከፍተኛ እንደ ነበር የመረጃ ምንጮቻችን ገልጠውልናል። ከዚህ በተጨማሪ አጥቢያ ያላቸው መነኰሳት ለመሾም 500,000,00 (አምስት መቶ ሺህ) ከፍለው የተሾሙ ሲሆን በሠራዊት ታጅበው አዲስ አበባ የገቡ መሆናቸው ታውቋል።   

 



ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሶዶ ዳጬ ወረዳ የሚገኘው ሐሮ ቅዱስ ባለወልድና ቅዱስ ዑራኤል ገዳም


 

No comments:

Post a Comment

በሲሞን መንገድ ላይ ተገኙት “አባ” ወ/ኢየሱስ ኢፋ (ፍቅሩ ኢፋ) - ክፍል ሁለት

  እኚህ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን መጀመራቸው አያጠራጥርም። በዚህም የሕይወት ምርጫቸውንም ቅዱስ ጳውሎስ “እንደኔ ብትሆኑ እወዳለኹ” ያለውን ተከትለው በሙሉ ጊዜያቸው እግዚአብሔርን እያመሠ...