Friday, January 27, 2023

በኢትዮጵያ/ኦ/ቤ/ክ በምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ቄስ ለታ ደገፌ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ሕገ ወጥ አካላትን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ ነው።

በኢትዮጵያ/ኦ/ቤ/ክ በምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ቄስ ለታ ደገፌ ጥር 20 ቀን ሕገ ወጡን ቡድን ለመቀበል  በጊምቢ ከተማ በመዘዋወር በሞንታርቦ ታግዘው ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። የድምጽ ቅጁም ትርጉም እንደሚከተለው ነው።

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።”  ገላትያ 5፥1

የኦሮሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ! እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ማለትን እንፈልጋለን። የምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት ፣ ጊምቢ ከተማ ፣ በጊምቢ ከተማ ለሚትኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይዎች እና ለሌሎችም ለሁሉም ፤ ብፁዓን አባቶቻችን በጥር 14 ቀን ከኦሮሚያ ይነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች በሙሉ መልስ የተሰጠበት ከ20 የሚበልጡ ጳጳሳትን የሾምን ፣ ኦሮሚያ ውስጥ ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት መልስ የሰጡበት ያችን የተከበረች የተባረከች ቀን። ታዲያ ከእነዚህ ብፁዓን አባቶች ውስጥ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ለምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የተሾሙት በጥር 20 በዕለተ ቅዳሜ ከብፁዓን አባቶች ጋር ብዙ ሆነው ወደ ጊምቢ ከተማ ይመጣሉ። ሁላችሁም ወጥታችሁ እንዲትቀበሏቸው በዚህ ደስታችን ላይም እንዲትገኙ በእግዚአብሔር ስም ልናሳስባችሁ እንፈልጋለን። በኦሮሚያ ለሚገኙ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሉ ለብዙ ዘመናት ይጠየቅ ለነበረው ጥያቄ መልስ ተሰጥቶበታል። የኦሮሚያ ቅዱስ ስኖዶስ እነዚህን ጥያቄዎች በመስማት በኦሮሚያ ለሚገኙ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሉ መልስ ለመስጠት ጳጳሳትን እየሾመ ይገኛል። ለኦሮሚያ የተሾሙት ከ20 የሚበልጡ ጳጳሳት በቀን ጥር 20 በዕለተ ቅዳሜ በጊምቢ ከተማ አደራሽ ይገኛሉ። ሌሎች አማኞችም በዚህ ደስታችን ላይ እንዲትገኙ የተደሰትንበትን እንዲትደሰቱልን በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናቀርብላችኋለን። በድጋሚ እንኳን ደስአላችሁ ደስአለን ማለት እንፈልጋለን። የኦሮሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ! የምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት እንኳን ደስአላችሁ ደስአለን።"




No comments:

Post a Comment

በሲሞን መንገድ ላይ ተገኙት “አባ” ወ/ኢየሱስ ኢፋ (ፍቅሩ ኢፋ) - ክፍል ሁለት

  እኚህ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን መጀመራቸው አያጠራጥርም። በዚህም የሕይወት ምርጫቸውንም ቅዱስ ጳውሎስ “እንደኔ ብትሆኑ እወዳለኹ” ያለውን ተከትለው በሙሉ ጊዜያቸው እግዚአብሔርን እያመሠ...