Monday, February 20, 2023

በሲሞን መንገድ ላይ ተገኙት “አባ” ወ/ኢየሱስ ኢፋ (ፍቅሩ ኢፋ) - ክፍል ሁለት


 

እኚህ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን መጀመራቸው አያጠራጥርም። በዚህም የሕይወት ምርጫቸውንም ቅዱስ ጳውሎስ “እንደኔ ብትሆኑ እወዳለኹ” ያለውን ተከትለው በሙሉ ጊዜያቸው እግዚአብሔርን እያመሠገኑ ለመኖር ወስነው መንኩሰዋል። ግን ለዓለም አልሞቱም። ከክርስቶስ ፍቅር ይልቅ በዘራቸው ፍቅር ተለከፉ፣ከትህትና ይልቅ ትዕቢትን ገንዘብ አደረጉ። እራስን ዝቅ በማድረግ ከሚገኝ አምላካዊ ጸጋ ይልቅ በሰይጣን መንገድ ሄደው መከበርን ሻቱ፣አቦ አቦ መባል ናፈቃቸው። ስለዚህም በእነ ዋስይሁን አመኑና በገረመው አፈወርቅ ፖለቲካ ተጠለፉ። በአፋን ኦሮሞ እያገለገሉ አይናቸውን በጨው አጥበው “የኦሮሞ ሕዝብ በቋንቋው አይገለገልም።” ብለው ዋሹ። እውነታው ግን የሌላ ብሔር ተወላጅ የሆኑ አገልጋዮችን ማየት አለመፈለጋቸው እንደሆነ አብረዋቸው የኖሩ ሰዎች ጠንቅቀው የሚያውቁላቸው ጾራቸው ነው። 

 እንኳንስና እስከ መመንኮስ የደረሰ አገልጋይ ካህን፤ የትኛውም ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን የሰው ልጆችን ልዩነት አክብሮ በሰውነታቸው የሃይማኖት፣የብሔር፣የሀብት፣የዕውቀት ወዘተ ልዩነት ሳያደርግ “ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ” ያለውን የጌታ ቃል እንዲፈጽም ግድ የሚለው ሃይማኖታዊ ህሊና ገንዘብ ያደረገ ነው። እኚህ ሰው ግን በጥላቻ የተሞሉ፣ነፍሰ ገዳዮችን በሀሳብ፣በገንዘብ እና በቁሳቁስ የሚደግፉ፣የኦሮሞ መንግስት ተሹሟል። አሁን ጊዜው የእኛ ነው በማለት ተስፋቸውን ከእግዚአብሔር አንስተው ምድራዊ መንግስትን የተደገፉ አሳዛኝ ሰው ናቸው።

የቀድሞው አባ ወ/ኢየሱስ ኢፋ እጅግ ሲበዛ ክብርን የሚፈልጉ የሁሉ አባት ከመሆን ይልቅ የአንድ ብሔር አባት መሆንና መባል የሚፈልጉ፣እጅግ ሲበዛ እልከኛ፣በድሎ ይቅርታ መጠየቅንም ሆነ ተበድሎ ይቅር ማለትን እንደውርደት የሚቆጥሩ ቅዱስ ጳውሎስ ፡ምናልባት ስለ እናንተ በከንቱ ደክመን ይሆናል።” ብሎ እንደተናገረው በከንቱ የተደከመባቸው ሰው ናቸው። ካላቸው የፖለቲካ አመለካከት የተነሳም በገረመው አፈወርቅ መልማይነት የዋስይሁን አመኑ የፖለቲካ ካድሬ ለመሆን የበቁ የኦሮሞ ነጻውጪ ታጋይ መነኩሴ ናቸው።

እኚህ ሰው ቀሚስ አጥልቀው፣ቆብ ደፍተው፣ጺማቸውን አንዠርገው ሲታዩ ለተመልካች የሃይማኖት አባት ይምሰሉ እንጂ ፈጽሞ ኦርቶዶክሳዊነት ያልገባቸው፣እንዲገባቸውም የማይፈልጉ ሲበዛ በራስ አምልኮ የተጠመዱ እና በድፍረት ሐጢያት ለመስራት ወደኋላ የማይሉ ግብዝ ሰው ናቸው። እውነት ለመናገር እንደነዚህ ያሉ አባቶች/ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ቤተክርስቲያንን ለማገልገል የወሰኑ፣የአብነት ትምህርት በመጠኑም ቢሆን የቀጸሉ/ ሲገኙ እንደ አንድ ልጅ በስስት የሚታዩ የዋሁን የምዕራብ ወለጋ ምዕመናንን በተኩላ ከመነጠቅ የሚያድኑ እውነተኛ እረኞች ይሆናሉ ብሎ ተስፋ ያልጣለባቸው በእነሱም ያልተደሰተ ሃይማኖት ወዳድ ምዕመን እና የቤተክርስቲያን አባት አልነበረም።

ሆኖም ግን እነሱ ፖለቲከኞች በፈጠሩት የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት አዕምሯቸው የታጠበ ለእውነት ቆሞ ጽድቅን ከመስራት ይልቅ በጎጥ ፖለቲካ ውስጥ ተዘፍቀው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ፀጋ ተነጥዋል። ከክብርም ተዋርደዋል። እውነት ለመናገር እነኚህ ሰዎች ምንም የሃይማኖት ጥብቅና የሌላቸው፣እንቆምለታለን የሚሉትን የኦሮሞ ሕዝብ ለማገልገል ዕውቀቱም ፍላጎቱም የሌለቻው ናቸው። ለመንግስትም ሆነ ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ ልባቸውን ያከበዱ እልከኞች ናቸው። መንግስትን ያስቀደምኩት በእነሱ እምነት አሁን ላይ ሁሉን አድራጊና ፈጣሪ ምድራዊ መንግስታቸው እንጂ የሰማይ አምላክ አይደለምና ነው።

ሰሞኑን “አይዟችሁ ከጎናችሁ ነኝ አንዳች አትፍሩ።” በማለት የልብ ልብ ሲሰጣቸው የከረመው መንግስት የሾሟቸው ጳጳሳት ይቅርታ ጠይቀው እንዲመለሱ ሲያደርግ፣ጓደኛቸው የቀድሞው አባ ገ/ማርያም “የበሬ ወለደ ተረት” ነው ብለው “መንግስትን ውሸታም ነህ” ሲሉት አላፈሩም። አሁን በተጨባጭ እነ ዋስይሁን አመኑ የሰጧቸውን ፖለቲካዊ ተልዕኮ ለመፈጸም የማንም ቋንቋ ያልሆነውን ግዕዝን ማጥፋት አለብን ብለው ዘመቻ ጀምረዋል። ጥቂት ደጋፊዎቻቸውንም ሰብሰብው አስጨብጭበዋል። ምንም እንኳን ቅዱስ ሲኖዶስ፣መንግስትና አፈንጋጭ ጳጳሳቱ የተስማሙበትን ሳይሸራረፍ ተቀብለናል ብለው የጋራ መግለጫ ቢያወጡም፣ በትረ ሙሴ ስለያዙ ከገበያ የተገዛ የጳጳሳትን አስኬማ ስለደፉ እና ሙስሊምና መናፍቅ ለፖለቲካ ፍጆታ በመንግስት ድጋፍ ወጥቶ ስለተቀበላቸው፣ “ካፈርኩ አይመልሰኝ” በማለት በወረራ የያዙትን መንበረ ጵጵስና አልለቅም ሲሉ ተደምጠዋል።

ለሚያስተውል የትኛውም ምዕመን እንዲህ እንዲህ እናደርግላችኋለን በማለት ከሚዋሹት ውሸት በላይ ከሥራቸው ብዙ መማር ስለሚቻል ምዕመናኑ ወደ ቀልባቸው ተመልሰው ከእነዚህ አቶዎች እጅ መስቀል እንዳይሳለም እነሱ በሚገኙበት አጥብያ ባለመገኘት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ሊያከብር ይገባል። መልዕክታችን ነው።

    ቋንቋ አንዳችን ከሌላችን ጋር እንግባባበት ዘንድ ከእግዚአብሔር የተሰጠን የመግባብያ መሳርያ ነው። አንድ ቋንቋ ከሌላው ቋንቋ የሚበልጥበት አንዳች ምክንያት የለም። እርኩስና ቅዱስ የሚባል ቋንቋ የለም። ቋንቋ በጠባዩ ባለቤት የለውም ይባላል። ምክንያቱም ቋንቋ በመወለድ/በዘር/ የሚወረስ ሳይሆን በትምህርትና በልምምድ የሚገኝ ክህሎት ነው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው አንድ ከጉራጌ ቤተሰብ የተወለደ ህጻን ትግራይ ክልል ውስጥ ቢያድግ ያለጥርጥር የአፍ መፍቻ ቋንቋው ትግርኝ እንጂ ጉራግኛ ስለማይሆን፤

ማንኛውም ሰው በአፍ መፍቻ ቋንቋው ወንጌልን መማሩ የሚጠቅመው “ሒዱና ዓለምን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀመዛሙርት አድርጓቸው” ያለውን የጌታ ቃል መፈጸም ስለሆነ በቀዳሚነት ቤተክርስቲያንን ነው። በሐዋርያዊ ተልዕኮ ትምህርቷም ውስጥ አማኞችን በሚሰሙት ቋንቋ ማስተማር አጽንዖት የሚሰጠው የትምህርት ክፍል ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህ ብዥታ ያለው አንድም ሰው ያለ አይመስለኝም። ነገር ግን በቋንቋ ማስተማርን እንደምክንያት ወስዶ ሌላ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ማጃመል ግን እንኳንስ ለዓለም ሞቼያለኹ ከሚል መነኩሴ አይደለም ከየትኛውም ኦርቶዶክሳዊ አማኝ የሚጠበቅ አይደለም። ስለሆነም እነኚህ አካላት ከብዙ መመዘኛ አንጻር እንኳንስና ጳጳስ ቄስ ለመባል ብቁ ስላልሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ከስህተት እንይወድቅ በጥንቃቄ ጉዳያቸውን ማየት ይኖርበታል እንላለን። ይቆየን።

 

No comments:

Post a Comment

በሲሞን መንገድ ላይ ተገኙት “አባ” ወ/ኢየሱስ ኢፋ (ፍቅሩ ኢፋ) - ክፍል ሁለት

  እኚህ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን መጀመራቸው አያጠራጥርም። በዚህም የሕይወት ምርጫቸውንም ቅዱስ ጳውሎስ “እንደኔ ብትሆኑ እወዳለኹ” ያለውን ተከትለው በሙሉ ጊዜያቸው እግዚአብሔርን እያመሠ...