Tuesday, January 24, 2023

እየዳኸ ወርኃ ጥር የደረሰው መፈንቅለ ፓትርያርክ

ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ሲኖዶስ በኋላ ሦስቱ ጳጳሳት፣ በጉዳዩ ላይ እጃቸው ያለበት አንዳንድ የብልጽግና ባለሥልጣናት፣ ከቀሲስ በላይ ጋር የኦሮምያ ቤተ ክህነት አንቀሳቃሽ የነበሩ አንዳንድ አካላት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የአቡነ ኤዎጣቴዎስ መኖሪያ ቤት ውስጥ እየተሰበሰቡ ይመክሩ ነበር። ጉዳዩን በበላይነት ይመራ የነበረው የኦሮምያ ቤተ ክህነት አቀኝቃኝ የነበረውና ከእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ጋር በመሆን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያኔ ተመለስኩ ብሎ የነበረው ዋሲሁን አመኑ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን ገልጠውልናል።

መፈንቅለ ፓትርያርክ አድራጊዎቹ በተለይ ከኅዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ቀኑን ሙሉ ተሰብስበው ይውሉ የነበረ ሲሆን ኅዳር 21 ቀን 11፡00 ሰዓት አካባቢ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ወጥተው አንድ አሳቻ ቦታ የኦነግ መስራች፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀኝ እጅ ከሆነው፣ በግል ተወዳድሮ የሕዝብ እንደራሴዎች አባል ከሆነው ከዲማ ነገዎ ጋር ተገናኝተው በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ ባይታወቅም መወያየታቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልጠውልናል።

 



ዶ/ር ዲማ ነገዎ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለሕክምና ከአገር ሲወጡ በተቀነባበረ መንገድ ጽላት ሰርቀው ለመውጣት ሙከራ እንዳደረጉ እና ይህ ድርጊት ሲከሽፍ አቡነ ሳዊሮስ አብረዋቸው እንዲሄዱ የተደረገውም በዓላማ አንድም በየጊዜው የሚያደርጉትንና ከእነማን ጋር እንደሚገናኙ፣ ምን እንደሚሠሩ ለመከታተል እና ምክንያት ፈጥሮ ከአገር እንደወጡ እንዲቀሩ ለማድረግ ቢሆንም ፓትርያርክ ማሳደዱ ስላልተሳካ ጥር 14 የተፈጸመውን ድሪጊት ወደ ማስፈጸሙ እንደተሸጋገሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኦሮሞ ብልጽግና፣ የኦነግ፣ የኦፌኮ አባላት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ባሉበት በተደጋጋሚ በስውር እየተሰበሰቡ ይመክሩ የነበረውም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ፓትርያርክ ለማድረግ ሳይሆን ለዓላማችሁ ደጋፊ አልሆንም በማለታቸው እስከ ግድያ እየዛቱባቸው የሚገኙትን ሊቀ ጳጳስ ፕትርክና ለማሾም ብቻ ሳይሆን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አሻሽለው ለእነርሱ በሚመች ማንም ሰው ጳጳሳትን የሚሾምበትን ሕግ ለማስቀመጥ ቢሆንም ሁሉም ተሰብሳቢ ሲስማማ የሰላም ምኒስቴር ዴኤታ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ ብቻ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምን አደረገችን? ተው ይህ ነገር አያዋጣም” በማለት እንደተናገሩም ለማወቅ ተችሏል።

በተደጋጋሚ ይወያይ የነበረው ስውር ቡድን ኅዳር 21 ቀን እንደሁል ጊዜው ዶ/ር አቡን ኤዎስጣቴዎስ መሪነት ወደ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ከመሄዳቸው በፊት ስለአቡነ አብርሃም ይችን ጎጃሜ ወደደችም ጠላችም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ነቅለን እንጥላታለን እኔ ዶክትሬቴን ተምሬ እንግሊዝኛ መናገር የማትችል ጳጳስ እይመራችን፣ አቡነ እስጢፋኖስን አቋም የላትም አስፈራርተን የዓላማችን ተባባሪ እናደርጋለን፣ ይችን ዘፋኝ አዝማሪ ናትናኤልን ዓላማችንን የማትቀበል ከሆነ እናስወግዳታለን፣ ሩፋኤል እሷ ከእኛ ጋር ነች በማለት ሲዝቱ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።  

 



ሽመልስ አብዲሳ

ኅዳር 21 ቀን ከዲማ ነገዎ ጋር የተወያየው አካል በሦስተኛ ቀኑ ኅዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ባለድርሻ የሚሏቸው የኦሮሞ የብልጽግና ባለሥልጣናት፣ ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች፣ የኦነግና የኦፌኮ አመራሮች በአቡነ ሳዊሮስ ሰብሳቢነት በእስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ማድረጋቸውንም ምንጮቻችን ገልጠውልናል። በሦስቱ ጳጳሳት የተደረገው ሲመት የመንግሥት ድጋፍ ያለው ለመሆኑ ሌላው ማሳያ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ሲመቱን ሊቃን ጳጳሳት እንዲያሳምን ከማድረግ በተጨማሪ እኔም ኦርቶዶክስ ነበርኩ አንዳንድ ነገሮች አልመቸኝ በማለታቸው ወጥቼ እንጂ በማለት የማገባባት ስራ እንዲስራ ሀላፊነት የወሰደ እና የኦሮምያ ቤተ ክህነትንም በገንዘብ ይደግፍ እንደነበር ይታወቃል። ሽመልስ አብዲሳ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ የመንግሥት ጋር የተጣላ መስሎ ከአገር የወጣው ድንቁ ደያስ አንድ ሙሉ ሕንፃ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።

አቶ ሌንጮ እና አቶ ገላሳ በሰጡት አንድ ሥልጠና ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአዳማ አዩ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተይዞላቸው ለሦስት ቀን ሲዶለቱ መሰንበታቸው ለማወቅ ተችሏል።

 

 

No comments:

Post a Comment

በሲሞን መንገድ ላይ ተገኙት “አባ” ወ/ኢየሱስ ኢፋ (ፍቅሩ ኢፋ) - ክፍል ሁለት

  እኚህ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን መጀመራቸው አያጠራጥርም። በዚህም የሕይወት ምርጫቸውንም ቅዱስ ጳውሎስ “እንደኔ ብትሆኑ እወዳለኹ” ያለውን ተከትለው በሙሉ ጊዜያቸው እግዚአብሔርን እያመሠ...