Saturday, January 28, 2023

አደባባይ እየውጣ ያለው የብልጽግና ስውር እጅ በቡኖ በደሌ

የቡኖ በደሌ ዞን አስተዳደር አቶ አማን ደኑ እና የዞኑ ድርጅት ቢሮ ኃላፊ አቶ አረጋ ሽጉጤ የበደሌ ወረዳ ሊቃነ ካህናት መላከ ብርሃንን፣ ቀሲስ አያሌው ነጋን እና ቀሲስ እንዳለው ከበደን ቢሮ ጠርተው ለቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተመደቡትን ሰው (በሕገ ወጥ የተሾሙትንና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ግለሰብ) መቀበል እንዳለባቸው ለዚህም የፕሮቴስታንት እና ሙስሊም ወጣቶችን አደራጅተናል፤ እስከ ጅማ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲመቻች አድርገናል በማለት በግድ እንዲቀበሉ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛል።



አቶ አማን ደኑ
አቶ አረጋ ሽጉጤ




የምእራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት በሕገ ወጥ የተሾሙትንና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ግለሰብ ለመቀበል በሚል ለብልጽግና ባለስልጣናት ጥሪ ማስተላለፍ ጀምረዋል።

የምእራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት ግምቢ ከተማ መንበረ ጵጵስና ቤተ ክህነት ሃላፊ የሆኑት ሀብታሙ በንቲ በሕገ ወጥ የተሾሙትንና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ግለሰብ ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነና በአቃባበሉ ላይ ለብልጽግና ባለስልጣናት የጥሪ ደብዳቤ መላክ ጀመረዋል። ይህ ሃገረ ስብከት በብጹእ አቡነ ሩፋኤል የሚመራ ሲሆን በቃል የተናገሩትን በተግባር እርምጃ በመውሰድ የሚያሳዩበት ትልቅ ስራ ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።




Friday, January 27, 2023

አደባባይ እየውጣ ያለው የብልጽግና ስውር እጅ

  •  በቅዱስ ሲኖዶስ ተውግዞ የተለየው ቡድን ዛሬ ከኦሮሚያ ክልል ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ጋር በዝግ ውይይት እያደረጉ ይገኛል። የውይይቱን ይዘት እንደደረሰን ይዘን እንመጣለን።
  •  “መቀመጫችሁን አዲስ አበባ ማድረግ አለባችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን።” ሺመልስ አብዲሳ
  •  አዲስ አበባና በአዲስ አበባ ያሉ አድባራትና ገዳማትን በቀጣይ የግጭት ቀጠና ለማደርግ እየተሰራ ይገኛል።

 በቅዱስ ሲኖዶስ ተውግዞ የተለየው ቡድን መቀመጫ መንበራቸውን በወለጋ ለማድረግ አስቀድመው ባቀዱት መሰረት እየተንቀሳቀሱ የነበረ ቢሆንም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ በኦሮሚያው ፕሬዝዳንት በተሰጠ መመሪያ በአዲስ አበባ እንዲያደርጉ ታዘዋል። ይህም በቀጣይ የቤተ ክርስቲያንን ሃብት መካፈል አለብን በሚል ሰበብ አዲስ አበባንና በአዲስ አበባ ያሉ አድባራትና ገዳማትን የግጭት ቀጠና ለማድረግ እየሰሩ ይገኛል።

ዘግይቶ በደረሰን መረጃ ሕገወጥ ሿሚዎቹና ተሿሚዎቹ ከሹመቱ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደደረሱ ለደህንነታቸው አመች ነው በማለት ከኋላ ሁኖ በሚዘውራቸው የብልጽግና መንግስት በተዘጋጀላቸው በኦሮሚያ ጠቅላይ ፖሊስ መምሪያ በሚገኝ ማረፊያ አስቀምጧቸው እንደነበር ታውቋል። በኋላ ላይ ለምን ወደ ሆቴል እንዲዛወሩ እንደተደረገ የታወቀ ነገር የለም።




በኢትዮጵያ/ኦ/ቤ/ክ በምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ቄስ ለታ ደገፌ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ ሕገ ወጥ አካላትን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ ነው።

በኢትዮጵያ/ኦ/ቤ/ክ በምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ቄስ ለታ ደገፌ ጥር 20 ቀን ሕገ ወጡን ቡድን ለመቀበል  በጊምቢ ከተማ በመዘዋወር በሞንታርቦ ታግዘው ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። የድምጽ ቅጁም ትርጉም እንደሚከተለው ነው።

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።”  ገላትያ 5፥1

የኦሮሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ! እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ማለትን እንፈልጋለን። የምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት ፣ ጊምቢ ከተማ ፣ በጊምቢ ከተማ ለሚትኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይዎች እና ለሌሎችም ለሁሉም ፤ ብፁዓን አባቶቻችን በጥር 14 ቀን ከኦሮሚያ ይነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች በሙሉ መልስ የተሰጠበት ከ20 የሚበልጡ ጳጳሳትን የሾምን ፣ ኦሮሚያ ውስጥ ለሚገኙ አብያተክርስቲያናት መልስ የሰጡበት ያችን የተከበረች የተባረከች ቀን። ታዲያ ከእነዚህ ብፁዓን አባቶች ውስጥ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ለምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት የተሾሙት በጥር 20 በዕለተ ቅዳሜ ከብፁዓን አባቶች ጋር ብዙ ሆነው ወደ ጊምቢ ከተማ ይመጣሉ። ሁላችሁም ወጥታችሁ እንዲትቀበሏቸው በዚህ ደስታችን ላይም እንዲትገኙ በእግዚአብሔር ስም ልናሳስባችሁ እንፈልጋለን። በኦሮሚያ ለሚገኙ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሉ ለብዙ ዘመናት ይጠየቅ ለነበረው ጥያቄ መልስ ተሰጥቶበታል። የኦሮሚያ ቅዱስ ስኖዶስ እነዚህን ጥያቄዎች በመስማት በኦሮሚያ ለሚገኙ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሉ መልስ ለመስጠት ጳጳሳትን እየሾመ ይገኛል። ለኦሮሚያ የተሾሙት ከ20 የሚበልጡ ጳጳሳት በቀን ጥር 20 በዕለተ ቅዳሜ በጊምቢ ከተማ አደራሽ ይገኛሉ። ሌሎች አማኞችም በዚህ ደስታችን ላይ እንዲትገኙ የተደሰትንበትን እንዲትደሰቱልን በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናቀርብላችኋለን። በድጋሚ እንኳን ደስአላችሁ ደስአለን ማለት እንፈልጋለን። የኦሮሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ! የምዕራብ ወለጋ ሃገረ ስብከት እንኳን ደስአላችሁ ደስአለን።"




Thursday, January 26, 2023

የሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስና መሐንዲሶች

የዘር ፖለቲካ በሀገራችን ማቀንቀን ከጀመረ ሦስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ረጅም ጊዜ ውስጥ ጽንፈኛ ኃይሎች የመጀመርያ ኢላማቸው ካደረጓቸው ተቋማት ውስጥ አንደኛዋና ዋነኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ በግልጽ የሚታይ ሀቅ ነው።

እንደማሳያ ጥምጣማቸውን ጠምጥመው ለአገልግሎት የሚንቀሳቀሱ ካህናት አባቶችን እንደ ሃይማኖት አባት ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ካድሬ እንዲቆጠሩ ለማድረግ እንዲህ እያሉ የማጠልሸት ሥራ ሲሰሩ ቆይተዋል።  "dabbale mata addii biyya keenyarra badii." ትርጉሙ "ነጭ ራስ ካድሬ ከሀገራችን ጥፋ።" እና ወዘተ በማለት የዋኹን ምዕመን ከእምነቱ ለማስኮብለል ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።

በተለይ የፖለቲካ ርዕዮታቸውን ለማራመድ የተመቻቸው እና የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክታቸውን የተቀበላቸውን የምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና በአሁኑ አከላለል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ምዕመናን ተጠቃሽ ናቸው። ሆኖም ግን ባሰቡት ልክ በፖለቲካቸው ተጠልፈው እምነታቸውን ለቀው መናፍቅ ወይ ሙስሊም አልሆኑም። በዚህ የተበሳጩት ፖለቲከኞች ተልእኳቸውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሰርጎ ገቦችን በመመልመል  በፖለቲካቸው አጠመቋቸው።

ማመናቸውን ካረጋገጡ በኋላ እንዲታመኑ ግዳጅ ሰጧቸው። ከእነዚህ ምልምሎች አንዱ የሆነው ዋሲሁን አመኙ ሲሆን ይህ ግለሰብ ከሃይማኖቱ ይልቅ ለዘሩ የሚንጨረጨር፣ ናርሲሲት፣ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ አሁን ቤተክርስቲያንን ለመክፈል ህገ ወጥ ጳጳሳት እንዲሾሙ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ሲታገል የኖረው ምንም እውቀት ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ ጵጵስና እንዲሾሙ በተለይ ሁለት መነኮሳትን የመለመለ ፀረ ኦርቶዶክስና ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ግለሰብ ነው።

ፖለቲከኞቹ የሚሹትን ከሀገር የመከፈል ፍላጎት በቤተክርስቲያን በኩል ማሳካት ይቻላል ብሎ የሚያምው ዋሲሁን አመኙ፣ ለዚህ ዓላማው መሳካት ከዕውቀት ነፃ የሆኑ፣ የኢኮኖሚ እና የስነምግባር ችግር ያለባቸውን በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ያሉትን ካህናትና ዲያቆናትን በመመልመል በደካማ ጎናቸው እየገባ ለሰይጣናዊ ተግባሩ የሚጠቀም ግለሰብ ነው። መንግስት የሃገሪቱ ሕዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ፖሊሲ በማውጣቱ ምክንያት በምእራብ ወለጋ ያሉ ምእመናን ቅዳሴውን ሰምተው አሜን ማለት አለመቻላቸውን ያስተዋለው ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በእራሳቸው ተነሳስተው ከሚቀድሱ ብሎ በቅንነት በማሰብ ቅዳሴውን ተርጉሞ ሲሰጣቸው የሰው ሀሳብ በመስረቅ እና በፖለቲካ አክራሪነታቸው የሚታወቀው ምትኩ ተኮላ የሚባል ሰው (በነገራችን ላይ ይህ ግለሰብ "ኦሮሞና ኦርቶዶክስ" የሚል መጽሐፍ ጽፎ የኦርቶዶክስ ተወሕዶ ሃይማኖትን ከባህላዊው ዋቄፈና እምነት ጋር አቻ ለማድረግ የጣረ ለስሙ ቄስ ነኝ የሚል ዘረኛ ነው) ጋር በመሆን ዲ/ን ዳንኤል የተረጎመውን የኦሮምኛ ቅዳሴ ከኤች አይ ቪ መከላከያና መቆጣጠርያ በዘረፈው ገንዘብ አሳትሞ በማሰራጨት የሚታወቅ የአዕምሮ ሀብት ሌባም ነው። ይኼ ሰው ነው እንግዲህ ቤተክርስቲያንን ለሁለት ለመክፈል ሲጥር የቆየውና ጊዜው የኛ ነው በሚል ስሜት እና በማን አለብኝነት ህገ ወጥ ሿሚና ሹመኞች ፊት ፎቶ በመነሳት ፖለቲካዊ የመገንጠል ግቡን አሳክቼያለኹ በሚል አጋንንታዊ መንፈስ የሚጀነነው። ይቆየን እንመለስበታለን



ሰበር ዜና

  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሕገ ወጥ ጵጵስና ሿሚዎችንና ተሿሚዎችን አወገዘ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሳያውቀውና ሳይመክርበት በግል ፍላጎታቸው ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመናል በማለት መግለጫ ያወጡትን ሦስት ሊቃነ ጳጳሳትና ሕገ ወጥ ሹመት የተቀበሉ መነኮሳትን አውግዞ ለይቷል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ያልተወሰነ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን የመክፈል ሴራ የጠነሰሱት ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ልብ ገዝተው በይቅርታ ልብ ወደ ቤተ ክርስቲያን እስከሚመለሱ ድረስ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ተለይተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ያለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ሲመተ ጵጵስናን በጓሮ በር ለማግኘት የቋመጡት ሕገ ወጥ ተሿሚዎችም በውግዘት እንዲለዩ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል።



የጨለማው ቡድን ቀጣይ ዕቅድ

ካፈርሁ አይመልሰኝ በሚል ድርቅና ቅዱስ ሲኖዶስ በድርድር "የሾምናቸውን ኤጲስ ቆጶሳት" ካልተቀበለን የራሳችንን ፓትርያርክ መርጠን ንብረት ወደ መካፈል እንሔዳለን እያለ ያለው የእነ "አባ" ሳዊሮስ ቡድን ሌላ ሕገወጥ ሹመት ሊሰጥ መሆኑ ተሰምቷል።

ለዚህም ዓላማ ከተለያዩ ቦታዎች ሹመት ናፋቂ "መነኮሳትን" ሕገወጥ ቡድኑ ወደሚሰበሰብበት ቦታ እንዲከቱ ጥሪ ተላልፎላቸው በመግባት ላይ ይገኛሉ።


በሲሞን መንገድ ላይ ተገኙት “አባ” ወ/ኢየሱስ ኢፋ (ፍቅሩ ኢፋ) - ክፍል ሁለት

  እኚህ ሰው የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን መጀመራቸው አያጠራጥርም። በዚህም የሕይወት ምርጫቸውንም ቅዱስ ጳውሎስ “እንደኔ ብትሆኑ እወዳለኹ” ያለውን ተከትለው በሙሉ ጊዜያቸው እግዚአብሔርን እያመሠ...